The Sun Shines For All! ፀሐይ ለሁሉም ታበራለች!

Awesome Stories

Upcoming Events

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ

Tsehay Insurance S.C

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ለማከናወን እንዲቻል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ እና የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ እና ምርጫ አሰራር ደንብ መሰረት የቦርድ አባላት የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ በኩባንያው የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 01 ቀን 2015 ዓ.ም መመረጡ ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሰረት የተሰየመው የቦርድ አባላት የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባላትን ጥቆማ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SIB/32/2012 እና  SIB/48/2019፤ እንዲሁም በኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ የአሰራር ደንብ መሰረት ከሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ብቻ የሚቀበል ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ዕጩ የቦርድ አባላትን እንድትጠቁሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

  1. የፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክሲዮን የሆነ፤
  2. የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
  3. በሌላ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ያልሆነ፤
  4. ዕድሜ 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፤
  5. የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ፤ የኩባንያው ወይም ሌላ መድን ሰጭ ኩባንያ ሰራተኛ ያልሆነ፤
  6. የስራ ልምድን በሚመለከት በንግድ ስራ አስተዳደር፤ በአካውንቲንግ፤ በህግ፤ በኢንጅነሪንግ፤ በምጣኔ ሃብት፤ በፋይናንስ፤ በኦዲት፤ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ፤ በይበልጥም በመድን ስራ አመራር ወይም ተዛማጅ መስኮች ወዘተ በቂ የስራ ልምድ ያለው ፤
  7. የህግ ሰውነት ያለው ድርጅት በዕጩነት ሊጠቆም ይችላል፡፡የህግ ሰውነት ያለው ድርጅት ዕጩ ሲደረግ የህግ ሰውነት ያለውን ድርጅት በቦርድ የሚወክል የተፈጥሮ ሰው ዝርዝር መረጃ መገለጽ ይኖርበታል፡፡
  8. በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ዉጭ የእምነት ማጉደል ወይም የማጭበርበር ተግባር ያልፈጸመ፤ ለገንዘብ ተቋማትና ለተቆጣጣሪ አካል ሃሰተኛ መረጃ ያልሰጠ፤ የስነ-ምግባር ደንቦችን ባለማክበር የስነ-ሥርዓት እርምጃ ያልተወሰደበት፤ በሙስና ወንጀል ተከሶ ያልተፈረደበትና የመምረጥና የመመረጥ መብቱ ያልተገደበ፤
  9. የፋይናንሻል ጤናማነትን (Financial soundness) መስፈርት የሚያሟላ፤
  10. የትምህርት ደረጃ፤

ሀ. ቢያንስ 75% የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ያጠናቀቁ መሆን ይኖርባቸዋል፤

ለ. የቀሩት 25% እንዳስፈላጊነቱ ቢያንስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያጠናቀቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

 ማሳሰቢያ

  1. በወንድ ፆታ የተገለጸው ለሴት ፆታም ይውላል፡፡
  2. እጩ የቦርድ ተጠቋሚዎች ብዛት 21 ሲሆን ከእነዚህም መካከል 7ቱ ከኩባንያው ጠቅላላ የተፈረሙ አክሲዮኖች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ 2 በመቶ በታች የአክሲዮን ድርሻ ባላቸው ባለአክሲዮኖች ብቻ ሊጠቀሙ የሚገባ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 14 እጩዎች በሁሉም ባለአክሲዮኖች ሊጠቆሙ ይችላሉ፡፡
  3. ጥቆማ የሚደረግበትን ቅጽ አዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ ከብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው በፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት፤በሁሉም የፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ቅርንጫፎች፤ እንዲሁም ከኩባንያው ድረ-ገጽ www.tsehayinsurance.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. የተሞላው የጥቆማ ቅጽ አዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ ከብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው በፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ፤በፖስታ ሳጥን ቁጥር 56144 ወይም በኢሜል አድራሻ tsehayinsurancesc.gmail.com መጠቆም ይቻላል፡፡
  5. ለጥያቄና ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመቅረብ፤ በኢሜል አድራሻ:tsehayinsurancesc.gmail.com ወይም በስልክ ቁጥር +251116506630 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  6. ከመስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን ከወዲሁ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

    ***የፀሐይ ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ***

 

የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

 

  ፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር

Tsehay Insurance S.C

የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

የስብሰባ ጥሪ

 ለፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013  አንቀፅ 366(1)፣ 367፣ 393፣ 394 እና በኩባንያዉ መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 9 መሰረት የፀሐይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የኩባንያዉ ባለአክሲዮኖች በእለቱ በቦታዉ ተገኝተዉ እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪዉን በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡

የ11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፤

      1. ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም
      2. የጉባኤዉን አጀንዳዎች ማፅደቅ፤
      3. እ.ኤ.አ በ2021/2022 በጀት ዓመት የተሸጡ አዳዲስ አክሲዮኖችንና የአክሲዮን ዝዉዉሮችን ማሳወቅ እና አዲስ ባለአክሲዮን መቀበል፤
      4. እ.ኤ.አ የ2021/2022 በጀት ዓመትን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት መስማት፤
      5. እ.ኤ.አ የ2021/2022 በጀት ዓመትን የዉጭ ኦዲተሮች ሪፖርት መስማት፤
      6. ከላይ በተቁ.4 እና በተ.ቁ 5 በቀረቡት ሁለት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
      7. በዘመኑ የተጣራ የትርፍ አደላደል እና አከፋፈልን በሚመለከት ተወያይቶ መወሰን፤
      8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና ምርጫ የሚያከናዉን የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ፤
      9. የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ወርሃዊ አበል ክፍያን መወሰን፤
      10. እ.ኤ.አ ከ2022/2023 ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት አገልግሎት የሚሰጡ የዉጭ ኦዲተሮችን መሾም እና የ2022/2023 የአገልግሎት ክፍያቸዉን መወሰን፤
      11. እ.ኤ.አ የ2021/2022 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ከተጣራ የትርፍ ድርሻ የሚታሰብ ክፍያን እና እ.ኤ.አ የ2022/2023 በጀት ዓመት ወርሃዊ አበል ክፍያን መወሰን፤
      12. የጉባኤዉን ቃለጉባኤ ማፅደቅ፡፡

 

ዋና ምዝገባ ቁጥር   MT/AA/3/0017159/2004 

የተከፈለ ካፒታል    292.10 ሚሊዮን

      • የዋና መስሪያ ቤት አድራሻ፤

አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 2185 ስ.ቁ.0116506630/38

ማሳሰቢያ፡

      • በጉባኤዉ ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች
      1. በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የተረጋገጠ እና በጉባኤዉ ላይ ለመካፈል የሚያስችል የዉክልና ስልጣን የተሰጠዉ ወኪል በእለቱ በጉባኤዉ ቦታ የዉክልና ሰነዱን ዋናዉን እና ቅጅዉን ይዞ በመገኘት በጉባኤዉ መካፈል ይችላል፡፡ ወይም
      2. ጉባኤዉ ከመካሄዱ ሶስት ቀናት በፊት በኩባንያዉ ዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ በግንባር ቀርበዉ ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀዉን የዉክልና ፎርም ሞልተዉ በመፈረም ተወካዩ ጉባኤዉን መካፈል ይችላሉ፡፡
      • ባለአክሲዮኖችም ሆነ ወኪሎች ወደ ስብሰባ ቦታ ሲመጡ ማንነታቸዉን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፤ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናዉንና ቅጅዉን ይዘዉ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የፀሐይ  ኢንሹራንስ  አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

ፀሐይ ለሁሉም ታበራለች!!!

 

Head Office Address

Bole Bridge, In front of Brass Hospital
Tel:+251- 111-11 97 70/71
Office:+251 - 116- 50 66 32/37/38
Fax: +251-111-11 98 86
Web: www.tsehayinsurance.com
E-mail: officemail@tsehayinsurance.com
P.O.Box: 56144

Quick Links

Products & Sevices

Newsletter

Subscribe our newsletter
to get latest updates